AMIGOS SAVING AND CREDIT COOP.

Instagram: https://instagram.com/amigossacco?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Facebook: https://www.facebook.com/Amigossacco

TikTok: tiktok.com/@amigossavingandcredit

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amigos-saving-and-credit-

View in Telegram

Recent Posts

በእውቅና እና በምስጋና መርሀ-ግብሩ ተጠናቋል።

(አሚጎስ የካቲት 3 ቀን 2017)

የኅብረት_ስራ_ኤግዚቢሽን-ባዛርና ሲምፖዚየም 2017ዓ.ም ተጠናቀቀ።

በኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮምሽን እና በአዲስ አበባ ኅብረት ስራ ኮምሽን በጥምረት  ከ ጥር 28- የካቲት 3 ቀን 2017ዓ.ም የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚየም በስኬት ተጠናቋል።

በከተሞች አካባቢ በግብርና ምርቶችና ሸቀጦች ላይ ለሚፈጠረው ያልተገባ የዋጋ ንረት ኀብረት ሥራ ማህበራት አምራቾችን ከከተማ ሸማቾች ጋር በቀጥታ የግብይት ትስስር በመፍጠርና አላስፈላጊ የግብይት እሴት ሰንሰለቶችን በማስቀረት ምርቶችና ሸቀጦች ለዜጎች ፍትሃዊ በሆነ የገበያ ዋጋ ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ እያደረጉ ያሉት ጥረቶች ተጠቃሽ  መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮምሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ኅብረት ስራ ኮምሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በመዝጊያ  መርሀ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ከ300 በላይ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ለግብይት በመቅረብ  አምራችና ተጠቃሚን በቀጥታ አገናኝተዋል ሲሉ ተደምጠዋል።

በመጨረሻም ለፕሮግራሙ መሳካት ከጎን ለሆኑ አጋር ድርጅቶች  የምስጋና እና እውቅና በመስጠት መርሀ-ግብሩ በደማቅ የመዝጊያ ስነ-ስርዓት ተጠናቋል፡፡

የኀብረት_ሥራ_ኤግዚቢሽንና ባዛር በደማቅ ስነ-ስርዓት ተከፈተ።

አሚጎስ ጥር 29 ቀን 2017

የኀብረት ሥራ ማህበራት ሚና ለኢትዮጵያ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል የኀብረት ሥራ ኤግዚቢሽንና ባዛር በደማቅ ስነስርዓት ተከፈተ።

በሀገር አቀፍ ለ11ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ለ4 ጊዜ ኤግዚቢሽን፤ ባዛርና ሲንፖዚየም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ በተገኙበት በደማቅ ስነስርዓት ተከፍቷል። እስከ የካቲት 3 ቀን 2017ዓ.ም የሚቀጥለው ኤግዚቢሽንና ባዛር ሸማቾችንና ተጠቃሚዎችን በቀጥታ እንደሚያገናኝ ተገልጿል።

ኀብረት ሥራ ማህበራት ለግብርና ምርታማነት ማደግ፣ ለምርት ዋጋ መረጋጋትና ለኢንዱስትሪ ዕድገት ከሚያደርጉት አስተዋጽኦ ባሻገር የፋይናንስ ተደራሽነትን በማሳደግና የስራ ዕድል በመፍጠር አይነተኛ ሚና እየተጫወቱ ናቸዉ ያሉት አምባሳደር ሽፈራዉ ሽጉጤ በዚህ መርሀ ግብር ከ350 በላይ የገጠር ግብርና ነክ እና የከተማ ሸማች ኀብረት ሥራ ማህበራት በሚያቀርቧቸው የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶች ያላቸውን ዕምቅ አቅም የምናይበትና ጉድለትና ጥንካሬያቸውን በመፈተሸ አቅማቸውን አሟጠን ለመጠቀም አስቻይ ሁኔታዎችን የምንገመግምበት ጊዜ ነው በማለት ገልፀዋል፡፡ 

በመጨረሻም አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ስራ ማህበር በኤግዚቢሽንና ባዛሩ ተሳትፎ በማድረግ ለተጠቃሚዎች አገልሎቱን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።

"የኅብረት ሥራ ማህበራት ሚና ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ሲንፖዚየም ተካሄደ።

   አሚጎስ (ጥር 28/2017ዓ.ም)

በኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን እና በአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን በጥምረት የተዘጋጀ ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲንፖዚየም የትብብርና የጋራ ዕድገት ልዩ መንፈስ አንጸባራቂ መድረክ ከጥር 28 እስከ የካቲት 3 ቀን 2017ዓ.ም ይካሄዳል።  ሁነቱ በሲንፖዚየም የተጀመረ ሲሆን  ኀብረት ሥራ ማህበራት በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች  በማጠናከርና የማህበረሰብ  አቅምን በማጎልበት ማኅበራዊ አኮኖሚ ዕድገት እንዲፋጠን ያላቸውን ዕምቅ አቅም የሚያሳዩበት መድረክ እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን ኅብረት ሥራ ማህበራት ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ለማህበረሰብ ተግዳሮቶች ምላሽ በመስጠት፣ ትብብርን በማጎልበት ለጋራ ዕድገትና ብልጽግና ሲታገሉ የቆዩ ናቸው፡፡

በሲንፖዚየሙ ላይ በክብር እንግድነት  ዶ/ር  ግርማ መንቴ የኢፌድሪ ግብርና ሚኒስቴር፤ ዶ/ር ሶፊያ ካሳ የግብርና ሚኒስቴር፤ አቶ ዣንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ፤ ዶ/ር ሸዋንጌ ሲፋ ከኢንተርናሽናል ኮፕሬቲቭ አሊያንስ(ICA)፤ አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ  የኢትዮጵያን ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮምሽነር፤ ወ/ሮ ልዕልት ግደይ የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮምሽነር፤ ወ/ሮ ማርታ ሃ/ማርያም  የብሄራዊ ባንክ ገዢ አማካሪ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ቋሚ ኮሚቴ፤ የኅብረት ሥራ ማህበራት ኃላፊዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

በዚህ ሲንፖዚየም ላይ 5 ጥናታዊ ፁሁፎች የቀረቡ ሲሆን ጥናቶቹም በአፍሪካ፣ በኢትዮጵያ እና በአዲስ አበባ ያሉ ህብረት ስራ ማህበራት ሚናን የሚዳስሱ ናቸው።
በመጨረሻም የፓናል ውይይት ተካሂዶ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

See more posts

View in Telegram