Arts Tv አርትስ ቲቪ

African Renaissance Television Service is an Ethiopian television news channel.
ARTS Media S.C.
Awlo Business Center
+251-11-657-7811
artstv.tv
[email protected]
subscribe: https://www.youtube.com/channel/UCSnwxtpNr-2QupM0qi11Y6Q?sub_confirmation=1

View in Telegram

Recent Posts

"የኢትዮጵያን ወጣቶች የራስ ምታት ለመፍታት ነው የመጣነው" የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ @ArtsTvWorld
የአፍሪካ ቆነጃጅት የሚፈኩበት ዝግጅት ጀመረ | Hub of Africa | ኩል @ArtsTvWorld
የድግስ ምግቦችን ቀለል ባለ መንገድ | ቅዳሜ ገበያ #ethiopian #ethiopia @ArtsTvWorld
ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራ እና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ግድቡን ለማጠናቀቅ 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው ተባለ።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ለግድቡ ቀሪ የግንባታ ሥራዎች 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል በሚል የተሰራጨው ዘገባ ለአሉታዊ ትርጉም የተጋለጠ ነው ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ጽ/ቤቱ አክሎም እንዲህ ያለ ውዝግብ ሊፈጠር የቻለው ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ እና የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማጠናከር ሀብት የማሰባሰብ ጥቅናቄ ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በተዘጋጀ መድረክ ላይ ከተገኙ ሚዲያዎች መካከል በጥቂቶቹ በተሰራጨ ያልተጨበጠ መረጃ መነሻነት እንደሆነ ጠቁሟል።

በተጨማሪም በዚሁ የጽ/ቤቱ መግለጫ ላይ ከመላው ህዝብ በተያዘው በጀት አመት 1.6 ቢሊዮን ብር ለማሰባሰብ መታቀዱን እና ፕሮጀክቱንም በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ሁሉም አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
ዳሽን ባንክ የሴቶችን አቅም ይበልጥ በማጎልበት ወደ ከፍተኛ አመራር እና ውሳኔ ሰጪ የስልጣን እርከን ለማምጣት የሚያስችለውን  መርሃግብር አስጀመረ።

የተቀናጀ የሴቶች አቅም ግንባታ ማስጀመሪያ መርሃግብር ያከናወነው ባንኩ መርሃግብሩ አካታችና ብዝሃዊ የስራ ድባብ ለመፍጠር የያዘውን እሴት በተግባር የሚያሳይበት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን አስታውቋል።

የመርሃግብሩ ዋና ዓላማ ሴት ሠራተኞቻቸውን በተሟላ መልኩ ማጎልበትና በባንኩ የአመራር ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ እንዲሁም ለወደፊት ብቁ የሆኑ ሴት አመራሮችን መፍጠር እንደሆነ የዳሽን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው አለሙ ተናግረዋል።

ዳሽን ባንክ በዛሬው ዕለት በይፋ ያስጀመረው የተቀናጀ የሴቶች አቅም ግንባታ መርሃግብር በሶስት አበይት ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ሊሰራ የተነደፈ ፕሮግራሙ መሆኑ ተገልጿል።

እነዚህም የሴት ሠራተኞች የትስስር ፕሮግራም ፣ የሴት አመራሮች የመተካካት ፕሮግራም እና የሴት ሠራተኞች የምክክር ፕሮግራም ናቸው ተብሏል።

ከደረጃ 5 እስከ ደረጃ 9 የስራ ሃላፊነት ላይ የሚሰሩና የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው ሴት ሠራተኞች ላይ በሚያተኩረው የሴት አመራሮች የመተካካት ፕሮግራም 70 የሚሆኑ ሴት ሠራተኞችን ወደ መጀመሪያ ደረጃ አመራር ፣ 35 ሴት ሠራተኞችን ወደ መካከለኛ እንደዚሁም ደግሞ 35 ሴት ሠራተኞችን ወደ ከፍተኛ አመራር ደረጃ ለማምጣት ማቀዱን ዳሽን ባንክ አስታውቋል።

ዳሽን ባንክ በስተመጨረሻም የሴት ሠራተኞቻችንን ይበልጥ የሚጎለብቱበትና የበለጠ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱበት እንዲሁም በከፍተኛ የራስ መተማመን የሚችሉበት የስራ ድባብ በጋራ እንፍጠር ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ቃልኪዳን ይጥና
#Dashen_bank#Artstvworld
ኢትዮ ቴሌኮም የ4ጂ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በመላው ሀገራችን በሚገኙ 67 ከተሞች አስጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም በመላ ኢትዮጵያ በሚገኙ 67 ከተሞች ለሚገኙ ደንበኞች ከፍተኛ ፍጥነት እና አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት ለማቅረብ ያስችላል ያለውን ዘመናዊ የ4ጂ LTE የሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን ገለጸ፡፡

የ4ጂ LTE ኔትወርክ ማስፋፊያው በከተሞቹ በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ ላይ የሚገኘውን የተጠቃሚዎቹን ፍላጎት መሠረት ያደረገ ነው የተባለ ሲሆን በቀጣይም በሌሎች የአገራችን ክፍሎች ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የቴሌኮም ኔትወርክ እና ዲጂታል መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡ #artst@Arts_tv
በሲኒማ ቆይታው በተመልካቾች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆት ያገኘው እና በአገር ውስጥ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሽልማቶችን ለማሸነፍ የበቃው "ዶቃ" ፊልም ለመጀመሪያ ጊዜ በአርትስ ቴሌቭዥን ብቻ ከምሽቱ አንድ ሠዓት እና ሦስት ሠዓት ላይ በተከታታይ ለዕይታ ይበቃል፡፡ የዚህን አጓጊ እና ተወዳጅ ፊልም 47 ሴኮንድ ቅንጭብ እንድትመለከቱ እንጋብዛኋለን #doka#ዶቃ#artstv#artstvworld
The brotherly people of Kenya celebrate their National Day tomorrow, December 12. African Renaissance Television from #AddisAbaba, #Ethiopia, extends its best wishes to #Kenya and Kenyans for a prosperous future. Heri ya Sikukuu ya Uhuru! Happy #JamhuriDay! መልካም የነፃነት በዓል፣ ኬንያ! #KenyaNationalDay#AfricanUnity#Prosperity#Celebration#Kenya#Ethiopia

The brotherly African people of Mauritania celebrate their National Day today, November 28. 🌍🇲🇷African Renaissance Television from Addis Ababa, Ethiopia, extends its best wishes to Mauritania and all Mauritanians for a prosperous future. Happy Independence Day, Mauritania!
Awash Bank announced revenue of 36.6 billion birr; the highest of all private banks in Ethiopia in the fiscal year; a 27% spike from the last. The 1st private bank established after the fall of the Dergue regime 30 yrs ago, this year Awash Bank earned a gross profit of 10.8 billon birr.

YouTube | Facebook | Instagram | TikTok | X
ADvTech ግሩፕ የፍሊፐር ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤትን በ7.5 ሚሊዮን ዶላር ለመግዛት ተስማማ

ADvTech ግሩፕ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የፍሊፐር ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤትን በ7.5 ሚሊዮን ዶላር ለመረከብ ከሥምምነት ደርሷል።

ሥምምነቱ አምስት ትምህርት ቤቶችን እና ሦስት ሺህ ተማሪዎችን የሚያካትት መሆኑ ተገልጿል።

የፍሊፐር ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት አምስት ካምፓሶች የሚገኙት በአዲስ አበባ በቅሎ ቤት እና ሰሚት አካባቢዎች ሲሆን በአምስቱ የትምህርት ቤቱ ቅርጫፎች አጠቃላይ ከ3 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ይገኙባቸዋል ተብሏል።

ግዥውን አስመልክቶ የADvTECH ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጄኦፍ ዋይት "በአፍሪካ ውስጥ ያለንን ተሳትፎ እያሰፋን እና በአህጉሪቱ የመማር እና የማስተማር መሪ በመሆን ያለንን ደረጃ በማጠናከር ፍሊፐር ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤትን ወደ ADvTECH ግሩፕ እንኳን ደህና መጣችሁ ስንል በደስታ ነው።” ብለዋል

በአካዳሚክ ልህቀት የሚታወቀው ፍሊፐር ኢንተርናሽናል ት/ቤት እ.ኤ.አ. በ1998 በወ/ሮ መና ሰላሙ በቀለ እና በወ/ሮ ሰርካዲስ ሰይፉ የተሻወርቅ የተመሰረተ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2018 መሥራቾቹ 85% ድርሻ ለጣና አፍሪካ ካፒታል እና ለሳሃም ግሩፕ መሸጣቸው ይታወሳል።

የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት አካል የሆነውን የተሽከርካሪ ማቆሚያ የስማርት ፓርኪንግ ሲስተም በሸገር ከተማ በይፋ አስጀመረ።

የስማርት ፓርኪንግ ሲስተሙ በአቅራቢያ የሚገኙ የፓርኪንግ ቦታዎችን ከማወቅ ባሻገር ያልተያዘ የማቆሚያ ቦታን በቀላሉ በመለየት ተሽከርካሪ ለማቆም የሚያጠፉትን ጊዜ እና ጉልበት ለመቀነስ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ አስተማማኝ አገልግሎት ለማግኘት፣ ትክክለኛ ተመን ያለው የአገልግሎት ክፍያ በቴሌብር በመፈጸም ከተጋነነ የአገልግሎት ክፍያ እና ከዚሁ ጋር ተያይዘው ከሚመጡ አለመግባባቶች፣ ካልተገባ ወጪ እና እንግልት ይጠብቃቸዋል የተባለ ሲሆን በቴሌብር የክፍያ ደረሰኝ ለማግኘት ያስችላቸዋልም ነው የተባለው።

የስማርት ፓርኪንግ ሲስተሙ የከተማው አሥተዳደር ሕጋዊ የፓርኪንግ አገልግሎት ሰጪዎችን በአግባቡ ለመለየት እና ወደሕጋዊ ማዕቀፍ ያልገቡትን ለማስገባት፣ ከመኪና ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ህገወጥነቶችን ለመቀነስ እና ለመቆጣጠር፣ የአገልግሎት ሰጪዎችን መረጃ በቀላሉ በኦንላይን በማግኘት ቀልጣፋ አሠራርን እንደሚዘረጋም ተነግሯል።

የስማርት ፓርኪንግ ሲስተሙ ለስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች በቴሌብር ሱፐርአፕ ሾፌር መተግበሪያ እንዲሁም ለመደበኛ የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ባለሙያዎቹ የፓርኪንግ አገልግሎት ጥያቄን/ትዕዛዝ ለመቀበል የሚያስችላቸው የባለሙያ ሲስተም አለው፡፡

ይኸው አገልግሎት ስማርት የሞባይል ቀፎ ወይም መተግበሪያ የሌላቸው ተገልጋዮች በአጭር ቁጥር መልዕክት አማካይነት አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል።

See more posts

View in Telegram