BBC AMHARIC ቢቢሲ አማርኛ

ይህ ገፅ በዋነኝነት የቢቢሲ አማርኛ፣ እንዲሁም የሌሎች ዓለም አቀፍ ዜና ወኪሎች ዘገባ ከነማስፈንጠሪያ (link) የሚቀርብበት የቴሌግራም ገፅ ነው፡፡

View in Telegram

Recent Posts

ትግራይ፡ ኢሰመኮ ወደ ማይካድራ የምርመራ ቡድን መላኩን አስታወቀ https://www.bbc.com/amharic/news-54920173
የሰሜን ኮሪያና የሩሲያ የመረጃ መዝባሪዎች ጥቃት በክትባት ምርምሮች ላይ https://www.bbc.com/amharic/news-54915504
የአሜሪካ ምርጫ፡ የትራምፕ መሸነፍ አረብ አገራትን ለምን አስደነገጠ? https://www.bbc.com/amharic/news-54917272
ጦርነት ተቃዋሚ ሰልፎች በበርሊንና በዴንቨር https://amharic.voanews.com/a/berlin-Denver-demo-11-13-2020/5660108.html በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና በህወሓት መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በአፋጣኝ እንዲቆም ግፊት እንዲደረግ የጠየቁ የትግራይ ተወላጆች ማኅበረሰቦች አባላት ጀርመን ዋና ከተማ በርሊን እና ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥም ኮሎራዶዋ ዴንቨር ከተማ ላይ ትናንት ሰልፎች አካሄደዋል።


ፍራንክፈርት የሚገኙት የትግራይ ተወላጆች ማኅበረሰቦች ጥምረት ሊቀመንበርና የሰልፉ አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ግርማይ በርኸ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል በሰልፉ ላይ ከተለያዩ አካባቢዎች የተጓዙት የሰልፉ ተሣታፊዎች ጥያቄዎቻቸውን ለቻንስለር አንጌላ መርከል ቢሮ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።


በሌላ በኩል ደግሞ ላለፉት ሃያ ስምንት ዓመታት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የዴንቨር ኮሎራዶ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሂሩት ሃጎስም ትናንት ከሺህ በላይ እንደሚሆኑ የገለጿቸው የትግራይ ተወላጆች በዴንቨር ከተማ ካፒቶል ሂል አካባቢ ሰልፍ ማድረጋቸውንና ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የአየር ድብደባውም እንዲቆም፣ የኤሌክትሪክና የስልክ አገልግሎቶች እንዲከፈቱ መጠየቃቸውን ተናግረዋል። “ዋናው ጥያቄአችን ጦርነት እንደማንፈልግ እንዲታወቅልን ነው” ብለዋል።


ፌደራሉ መንግሥት “በተወሰኑ የህወሓት ባለሥልጣናት ላይ እየተካሄደ ያለ ህግን የማስከበር እንቅስቃሴ” ብሎ የሚጠራው ሲሆን የህወሓት ባለሥልጣናት ግን “በትግራይ ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው” ይላል።


ከዶ/ር ግርማይ በርኸና ከወ/ሮ ሂሩት ሃጎስ ጋር የተደረጉትን ቃለምልልሶች ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።






 
በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች የድጋፍ ሰልፍ ተደረገ https://amharic.voanews.com/a/oromia-11-13-2020/5660040.html በኦሮምያ የተለያዩ አከባቢዎች ህወሓትን እና የሰሩትን
ለሃገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ - አዲስ አበባ https://amharic.voanews.com/a/blood-donation-drive-11-13-2020/5660036.html በግዳጅ ላይ ላለው ለሃገር መከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ድጋፎች እየተደረገ ነው። የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ በአስራ አንድ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ አመራሮችና የከተማው ነዋሪዎች ደግሞ ለመከለላከያ ሰራዊቱ ደም ለግሰዋል።


የሀገር ሉዓላዊነት ለማስከበር መስዋዕትነት እየከፈለ ያለውን ሰራዊት አስፈላጊ በሆነው ሁሉ መደገፍ አለብን ሲሉ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።


ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡






 
የትግራይ ክልል ከ10 ሺሕ ጦር በላይ መማረኩን አስታወቀ https://amharic.voanews.com/a/tigray-statement-11-13-2020/5659963.html - ተከዜ የአውሮፕላን ድብደባ ተፈፅሞበታልም ብሏል

- ፌዴራል መንግሥቱ መረጃው
የአምነስቲ ሪፖርት በማይካድራ ጭፍጨፋ https://amharic.voanews.com/a/5659913.html ማይካድራ ውስጥ በመቶዎች ሲቪሎች ላይ ጭፍጨፋ ለመካሄዱ ማስረጃ እንዳለው አምነስቲ አስታወቀ።ድርጊቱ በትግራይ የፀጥታ ኃይሎች ስለመፈፀሙ መረጃዎች ያመለክታሉ ሲል ያነጋገራቸውን እማኞች ቃል ጠቅሶ በሪፖርቱ ላይ አስፍሯል።የትግራይ ክልል በትግራይ ሕዝብ ላይ የተጀመረው ከባድ የዘር ማጥፋት ወረራን ለመቀጠል ሆን ተብሎ የተሰራጨ የሐሰት ዜና ነው ብሎታል። በአካባቢው የነበረ የህወሃት ልዩ ሃይልና ሚሊሻ የፈጸመው ጅምላ ጭፍጨፋ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል:
አምነስቲ ስለማይካድራዉ ጭፍጨፋ ማስረጃ ደርሶኛል አለ  በምዕራባዊ ትግራይ  ሁመራ አቅራቢያ “ማይካድራ” በተባለ አካባቢ የህወሓት ልዩ ኃይል ባልታጠቁ ዜጎች ላይ አሰቃቂ እልቂት መፈፀሙን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዉ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘ። ድርጅቱ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ፤ ሲቪል ነዋሪዎች የተገደሉት በስለት በአሰቃቂ ሁኔታ በህወሓት ታማኝ ኃይሎች ነዉ። https://www.dw.com/am/አምነስቲ-ስለማይካድራዉ-ጭፍጨፋ-ማስረጃ-ደርሶኛል-አለ/a-55596681?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss
የተባበሩት መንግሥታት የማይካድራዉን ጭፍጨፋ እንዲጣራ ጠየቀ የተባበሩት መንግሥታት ቃል-አቀባይ ሩፐር ኮልቪሌ የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ዘገባን ተከትሎ ለዶቼቬለ ለዶቼ ቬለ እንደገለጹት የማይካድራዉን ወንጀል የጦር ወንጀል ብሎ ለመፈረጅ ማጣራት ያስፈልጋል። https://www.dw.com/am/የተባበሩት-መንግሥታት-የማይካድራዉን-ጭፍጨፋ-እንዲጣራ-ጠየቀ/a-55597054?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss
በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን የአዉሮጳ ኅብረት ያቀረበዉ ጥሪ  ህወሓትን እየፈፀመ ያለዉን ግፍ ለማብቃት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ትግራይ ላይ የገጠመዉ ጦርነት እንዳሳሰበዉ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እየገለፀ ነዉ። የአዉሮጳ ኅብረት የዉጭ ጉዳይ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሪል በዚሁ ጉዳይ ላይ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን አነጋግረዋቸዋል ተብሎአል። https://www.dw.com/am/በኢትዮጵያ-ሰላም-እንዲሰፍን-የአዉሮጳ-ኅብረት-ያቀረበዉ-ጥሪ/a-55595010?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss
ተስፋ ሰጪው የኮሮና ወረርሽኝ ክትባት  ፊዘር እና ባዮቴክ  የተባሉ ሁለት የመድሃኒት አምራች ኩባንያዎች በዚህ ሳምንት ተስፋ ሰጭ የተባለ የኮሮና ተዋህሲ ክትባት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል። ምንም እንኳ ክትባቱ ሶስተኛ ደረጃ ሙከራ ላይ ያለ ቢሆንም ሀገራት ክትባቱን ለመግዛት እተረባረቡ ነው።የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽንም 300 ሚሊዮን ክትባቶችን ለማግኘት ተሰምቷል። https://www.dw.com/am/ተስፋ-ሰጪው-የኮሮና-ወረርሽኝ-ክትባት/a-55594374?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss
የመቐለ ወቅታዊ ሁኔታ እና የዛሬ ቅኝት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና የትግራይ ክልል መንግስት ወደ ጦርነት ከገቡ በኃላ በመቐለ ኑሮ ምን ይመስላል ? ነዳጅ ዘይት ጠፍቶአል። ኑሮ ተወዶአል። ነዋሪዎች በቻሉት ሁሉ የምግብ ቁሳቁስን እየሸመቱ ነዉ። ስልክ ተቋርጦአል። ኤሌክትሪክም ተቋርጦአል እየተባለ ነዉ። የመቀሌ ወኪላችን የከተማዋን ዉሎ ቅኝት ልኮልናል።  https://www.dw.com/am/የመቐለ-ወቅታዊ-ሁኔታ-እና-የዛሬ-ቅኝት/a-55596835?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss
የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት ጥቅምት 24 ቀን ዕኩለ ለሊት ገደማ በትግራይ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ልዩ ኃይል ጥቃት እንደደረሰበት ከተገለጸ በኋላ የተፋፋመው «ውጊያ» በማኅበራዊ ድረ-ገፆችም በርትቷል። የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ክልል ደጋፊዎች አንዳቸው በሌላቸው የበላይነት ለማግኘት በማኅበራዊ ድረ ገፆች ይተጋተሉ። https://www.dw.com/am/የማኅበራዊ-መገናኛ-ዘዴዎች-ቅኝት/a-55594950?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss
መስማት ለተሳናቸው ጭምብል የሠራችው ዲዛነር ሀናን  ከዲዛይነር ሀናን አህመድ የቅርብ ሥራዎች መካከል በተለይ መስማት ለተሳናቸው ሰዎች የሚጠቅም ጭምብል ይገኝበታል። ሀናን ከዚህ ቀደም በተለይ የሙስሊም ሴቶች አልባሳትን በባህላዊ መልኩ እያዘጋጀች በማቅረብ ትታወቃለች። https://www.dw.com/am/መስማት-ለተሳናቸው-ጭምብል-የሠራችው-ዲዛነር-ሀናን/a-55588428?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss
የትግራይ ክልል አዲሱ ጊዜያዊ አስተዳደር በፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት በትግራይ ብሔራዊ ክልል የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባፀደቀዉ ደንብ መሰረት ዶ/ር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሰየማቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል። https://www.dw.com/am/የትግራይ-ክልል-አዲሱ-ጊዜያዊ-አስተዳደር/a-55596942?maca=amh-rss-amh-news-1472-xml-mrss
ትግራይ፡ በማይካድራ የተገደሉ ሰዎች 'የጦር ወንጀል' ሊሆን እንደሚችል ተመድ ጠቆመ https://www.bbc.com/amharic/news-54933830
በርማ፡የአንግ ሳን ሱቺ ፓርቲ 'በአብላጫ' ድምፅ አሸነፈ https://www.bbc.com/amharic/news-54933828
የአሜሪካ ምርጫ፡በስተመጨረሻም ቻይና ጆ ባይደንን እንኳን ደስ አለዎት አለች https://www.bbc.com/amharic/news-54934137
ትግራይ ፡
See more posts

View in Telegram