DW Amharic
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Recent Posts
https://p.dw.com/p/4nch1?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾@dwamharicbot
👉🏾@dwamharicbot
በስፔን ቫሌንሲያ የተካሄደውን የማራቶን ውድድር በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ መገርቱ አለሙ ፤ በወንዶች ደግሞ ኬንያዊው ሰባስቲያን ሳቄ አንደኛ በመውጣት አሸነፉ። መገርቱ ውድድሩን ለማጠናቀቅ የፈጀባት ጊዜ 2 ሰዓት ከ 16 ደቂቃ ከ 49 ሰከንድ ሲሆን ዩጋንዳዊቷ ስቴላ ቼሳንግ ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያዊቷ ጡሩዬ መስፍን ሶስተኛ በመሆን አጠናቀዋል።
ዛሬ በወንዶች ማራቶን አሸናፊ የሆነው ኬንያዊው ሰባስትያን ሳዌ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት ከ 02 ደቂቃ ከ 05 ሰከንድ የፈጀበት ሲሆን ይህም በወንዶች የማራቶን ታሪክ አምስተኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል። 33 ሰከንድ ዘግየት ብሎ የገባው ኢትዮጵያዊ ደሬሳ ገለታ ውድድሩን ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ኬንያዊ ዳንኤል ማታይኮ ደግሞ ሶስተኛ ሆኗል። ኢትዮጵያዊው አትሌት ሲሳይ ለማ ያለፈውን ዓመት የቫሌንሲያ ማራቶን አሸናፊ ነበር ። አትሌቱ በወቅቱ በስፍራው ክብረ ወሰን ሆኖ በተመዘገበ 2:01:48 የገባበት ሰዓት ነበር።
በዛሬው የቫሌንሲያ ማራቶን አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ ከፓሪስ ኦሎምፒክ መልስ ከጉዳቱ አገግሞ መሳተፍ የቻለ ቢሆንም ነገር ግን ዉጤት አልቀናውም።
ዛሬ የቫሌንሲያ ማራቶን የተካሄደባት የስፔን ከተማ ከአንድ ወር በፊት ብርቱ የጎርፍ አደጋ ማስተናገዷ ይታወሳል።
በጎርፍ አደጋው 230 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን መንገዶች እና ቤቶች በጎርፍ ተወስደዋል ፣ ንብረትም ወድሟል።

ስለ አፍሪቃ ላይ ያለው የተጋነነ የፖለቲካ፣ የፖሊሲ እና የኢኮኖሚ አመለካከት ከስጋቶቹ አንዱ ነው። አፍሪቃ በጀርመን ሚዲያ በፖለቲካ ያለመረጋጋት፣ በሙስና፣ በደካማ መሠረተ ልማቶች፣ በቢሮክራሲያዊ መሰናክሎች ያሉባት ስለመሆንዋ ነዉ የሚሰማዉ። ይህ በእርግጥ የጀርመን ባለሃብቶችን፤ የጀርመን መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾችን ወደፊት እንዳይራመዱ ያግዳል። https://p.dw.com/p/4nbEM?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ስልጣናቸዉን ከመልቀቃቸዉ ጥቂት ቀደም ብሎ አፍሪቃን ለመጎብኘት የገቡትን ቃል እየፈፀሙ ነው። ጆ ባይደን ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የሚጎበኝዋት አፍሪቃዊትዋ አገር አንጎላ እንዲጎበኙዋት በአጋጣሚ አልተመረጠችም። https://p.dw.com/p/4nbMF?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የአዲስ አበባው ደንበኛችን ፋሲልን በስልክ አግኝተን አነጋግረናቸዋል። እንዲሁም የ 10 ዓመት ልጃችን ታግቶብን ከፍተኛ ችግር ላይ ነን ያሉን ሰው ጋርም ደውለናል። የሌሎች ተሳታፊዎችም አስተያየቶች ተካተዋል። https://p.dw.com/p/4naH2?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የሕዳር 21 ቀን 2017 የዓለም ዜና
• ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ከመንግሥታቸው የሚዋጉ ታጣቂዎች ”አንድ ሺሕ ዓመት ቢታገሉ ስለማያሸንፉን፤ ያኛውን መንገድ ጥለው ወደ ሰላም እንዲመጡ“ የሚል ጥሪ አቀረቡ።
• የኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከዩጋንዳው አቻቸው ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ከሶማሊያ ለማሸማገል እገዛ እንደሚያደርጉ አስታወቁ።
• በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ታጣቂዎች ዘጠኝ ሰዎችን ከመኖሪያ ቤታቸው በማውጣት ወደ ወንዝ ወስደው መግደላቸውን ተከትሎ “መንግሥት ለደህንነታችን ሊደርስ ይገባል” ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የሟቾች ዘመዶች ጥሪ አቀረቡ።
• ፈረንሳይ “ለጥናት እና ምርምር” በሚል ከ40 ዓመታት በላይ ይዛ ያቆየቻቸውን ወደ 3,500 የሚጠጉ የአርኪዮሎጂ ቅርሶች ለኢትዮጵያ አስረከበች።
• የሶርያ ተቃዋሚ ኃይሎች አብዛኛውን የአሌፖ ከተማ እንደተቆጣጠሩ መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው የሶርያ የሰብአዊ መብቶች ታዛቢ አስታወቀ።
• ፕሬዝደንት ቮሎዶሞር ዜሌንስኪ መንግሥታቸው የሚቆጣጠረው የዩክሬን ክፍል በሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን (NATO) ጥበቃ ሥር ከሆነ ሀገራቸው ከሩሲያ ጋር የሚደረገውን ጦርነት በተኩስ አቁም ለመቋጭት ልትስማማ እንደምትችል ተናገሩ።
ዜናውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕፉን ይጫኑ ፦
https://p.dw.com/p/4nboa?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መልካሙ ጌትነት ከወቅታዊ የክልሉ የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞም በርካታ ጤና ተቋማት መዘጋታቸውንና ሠራተኞች በስራ ገበታቸው እንደማይገኙ አስረድተዋል። https://p.dw.com/p/4nbQk?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
በጥናቱ መሰረት የኤች አይ ቪ ተሃዋሲ ስርጭት ላይ ይበልጥ ተጋላጭ የማህበረሰብ አካል በአፍላ እድሜ ላይ የሚገኙ ወጣት ሴቶች ናቸው፡፡ የተሃዋሲው የስርጭት ምጣኔም ከክልል ክልል ልዩነቶች ያሉት ቢሆንም አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ3.25 በመቶ የስርጭት ምጣኔ ከፍተኛው ነው፡፡ https://p.dw.com/p/4nbQW?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
“ በአጠቃላይ ወታደራዊ ድሮኖች ለአፍሪካ መንግስታት አማጽያንና አሸባሪዎችን ለማጥቃት ትልቅ አቅም ፈጥሮላቸዋል” ሚስተር ዊም ዝዌንበርግ መንግስታዊ ያልሆነውና በእንግሊዝኛ ምህጻሩ ፓክስ (PAX) የተስኘው የዳች የሰላም ድርጅት ተመራማሪ https://p.dw.com/p/4nbQA?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የቡና ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ
ዛሬ ቅዳሜ አዲስ አበባ ውስጥ ቡና አምራቾች፣ አዘጋጅቶ ሻጮች፣ አቀናባሪዎች፣ ላኪዎች እና ከቡና ልማት ጋር የተሰማሩ ኩባንያዎች በሸራተን አዲስ ሆቴል የቡና ዐውደ ርዕይ አድርገዋል።
ቪድዮ ዘገባ፤ ሰሎሞን ሙጬ

ኪጋሊ-ሩዋንዳ የአፍሪቃ ንፁሕ ከተማ
አዲስ አበባን ጨምሮ ብዙ የአፍሪቃ ትላልቅ ከተሞች የሚታወቁት በጫጫታ፣በሰዉ በመጨናነቅ፣ በቁሻሻ በመሞላታቸዉ ነዉ።የሩዋንዳ ርዕሰ ከተማ ኪጋሊ ግን ትለያለች።ከአፍሪቃ በጣም ንፁሕዋ ከተማ ናት።እንዴት ፀዳች?
ተከታዩን ቪድዮ ይመልከቱ