FBC (Fana Broadcasting Corporate)

This is FBC’s official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com

Recent Posts

ኢትዮ ቴሌኮም የዲ ኤስ ቲቪ ስትሪም ጥቅል ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ከመልቲ ቾይዝ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ዲ ኤስ ቲቪ ስትሪም ጥቅል የተባለ አገልግሎት ይፋ አድርጓል። ስምምነቱ ቀልጣፋ ፈጣንና በየትኛውም ጊዜና ቦታ የላቀ ጥራት ያላቸውን ይዘቶች በተለያዩ ስማርት ስልኮች ማግኘት የሚያስችል ነው። ጥቅሉ ከድምጽና ኢንተርኔት ግንኙነት በተጨማሪ የተለያዩ ተወዳጅ የስፖርት ቻናሎችን ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ ማየት…

https://www.fanamc.com/archives/287947
ለዒድ አል ፈጥር በዓል ይጠብቁን!
ጽንፈኞች ካስተላለፉት ሀሰተኛ መረጃ ዓላማ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት መፍጠር ነው – አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጽንፈኛ ሃይሎች ብርቱካን ተመስገንን በሚመለከት ያስተላለፉት የሀሰተኛ ዘጋቢ ፊልም ዋነኛ ዓላማ ትርምስና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት መፍጠር መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ተናገሩ። ሚኒስትሩ እንዳሉት፤ ሰሞነኛ የሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎች አንድምታ በቀላሉ የሚታዩ ሳይሆን የፖለቲካ አለመረጋጋት መፍጠር፣ ህዝብን በህዝብ ላይ ማነሳሳትና ግጭት የመፍጠር እኩይ ዓላማ ያነገቡ ናቸው። በኢቢኤስ…

https://www.fanamc.com/archives/287939
Live stream started
የዒድ አልፈጥር በዓል ልዩ ዝግጅቶችን በፋና ፖድካስት ይጠብቁን!
#ፋና_ፖድካስት
#fana_podcast
#ፋና_ሚዲያ_ኮርፖሬሽን
#Fana_Media_Corporation
ኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን በብርቱካን ተመስገን ዙሪያ ላስተላለፈው ዶክመንተሪ ይቅርታ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን በብርቱካን ተመስገን ዙሪያ ላስተላለፈው ዶክመንተሪ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

የኢቢኤስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አማን ፍስሐፅዮን ጉዳዩን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በድርጅቱ ውስጥ እና በውጭ የተቀናጀ ሃይል ከጋዜጠኝነት መርሕ ውጭ የሆነ ተግባር ተፈፅሟል ብለዋል።

https://www.fanamc.com/archives/287923
በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በሕዝቦች መካከል መጠራጠርን ለመፍጠር የሚጥሩትን መከላካል እንደሚገባ አስገነዘቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋራ በሆነች ሀገር በሕዝቦች መካከል መጠራጠርን ለመፍጠር የሚሹ አካላትን መከላካል እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡ ሚኒስትሩ ሰሞኑን በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በቀረበችው ብርቱካን ተመስገን ዙሪያ በሰጡት መግለጫ፤ መሰል አጠራጣሪ ሥራዎች በዋዛ እንደማይታለፉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ሰላም እንዳትሆን የሚፈልጉ አካላት እንዳሉ ጠቁመው፤…

https://www.fanamc.com/archives/287914
ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ተግባር ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በዝቋላ፣ ደሃና እና ሌሎች ወረዳዎች ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ተግባር ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አካባቢ ዝናብ አጠር በመሆኑ የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ ተግባርን ይሻል ብለዋል።

የተከዜን ተፋሰስ በመስኖ የማልማት ሥራም በየደረጃው የሚገኝ አመራር እና የአካባቢውን ማህበረሰብ ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን አስገንዝበዋል።

እኒዚህን ተስፋ ሰጭ ጅምር ሥራዎች ማጠናከር፣ ማስፋት እና በቀጣይነት መፈፀም እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የብሔረሰብ አስተዳደሩ ጅምር ተግባራት ለሌሎች ዝናብ አጠር የኢትዮጵያ አካባቢዎች ትምህርት ሰጭ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ተግባር ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በዝቋላ፣ ደሃና እና ሌሎች ወረዳዎች ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ተግባር ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አካባቢ ዝናብ አጠር በመሆኑ የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ ተግባርን ይሻል ብለዋል።

የተከዜን ተፋሰስ በመስኖ የማልማት ሥራም በየደረጃው የሚገኝ አመራር እና የአካባቢውን ማህበረሰብ ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን አስገንዝበዋል።

እኒዚህን ተስፋ ሰጭ ጅምር ሥራዎች ማጠናከር፣ ማስፋት እና በቀጣይነት መፈፀም እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የብሔረሰብ አስተዳደሩ ጅምር ተግባራት ለሌሎች ዝናብ አጠር የኢትዮጵያ አካባቢዎች ትምህርት ሰጭ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
የሴቶችን ጥቃት ለፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ መጠቀም ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ተግባር ነው – ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሴቶችን ጥቃት ለፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ መጠቀም ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ተግባር መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ሰሞኑን ብርቱካን ተመስገን ተብላ በምትጠራ ሴት ሀሰተኛ ታሪክ ላይ ተንተርሶ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚነሱ ሃሳቦችን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ማውገዝና…

https://www.fanamc.com/archives/287887
ሚኒስቴሩ ከብርቱካን ተመስገን ከበደ ጋር በተያያዘ ማብራሪያ ሰጥቷል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ በሆነችው ብርቱካን ተመስገን ከበደ የትምህርት ሁኔታ ጋር በተያያዘ ትምህርት ሚኒስቴር ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ የማብራሪያው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ስለሆነችው ብርቱካን ተመስገን ከበደ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ግንኙነት ስላለው ማብራሪያ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በስም ተጠቃሽ በ2012 ዓ.ም የ12ኛ…

https://www.fanamc.com/archives/287883
የፊቼ ጫምባላላ በዓል በስኬት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ የፊቼ ጫምባላላ በዓል በስኬት መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ ገለጹ፡፡ በዓሉ በተለይም በሐዋሳ ሶሬሳ ጉዱማሌ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በሚገኝበት የሚከበር በመሆኑ አስቀድሞ ዝግጅት መደረጉን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡ በዓሉ በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የክልሉ ማሕበረሰብ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን…

https://www.fanamc.com/archives/287876
Live stream finished (1 hour)
Live stream started
ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ያላቸውን ዘርፈብዙ ትብብር ለማጠናከር መከሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እና የደቡብ ሱዳን የገንዘብ ሚኒስትር እና ተጠባባቂ የነዳጅ ሚኒስትር ማሪያን ዶንግሪን (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም፤ የሁለቱን ጎረቤት ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት ሊያሳድጉ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ በተጨማሪም የሀገራቱን የሁለትዮሽ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ…

https://www.fanamc.com/archives/287873
See more posts