Gion Amhara
▫ማንኛውንም ጥቆማ ለመስጠት:-➛ @HaimonAb
Recent Posts
46 ንፁሃን ተጨፍጭፈዋል!
የብልጽግና ጦር በጎጃም ሰሜን ሜጫ ወረዳ ብራቃት ከተማና ዙሪዋ ስድስት ህጻናት፣ የሐይማኖት አባት፣ ሴቶችና አረጋውያንን ጨምሮ 46 ሰዎችን በግፍ ገድሏል። ግድያው የተፈጸመው የአገዛዙ ጦር ክፍሎች የሆኑት "መከላከያ ሰራዊት" እና "አድማ ብተና" እርስበርስ መዋጋታቸውን ተከትሎ ትናንት መጋቢት 22/2017 ዓ.ም እንደሆነ ታውቋል።
#Amhara#Ethiopia
የቲክቶክ ቻናላችን➲ tiktok.com/@amhara_gion

የአብን ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ዘሪሁን ገሰሰ ስለ አብን!
''አብን'' ስለተሰኘው የቀድሞ ድርጅታችን ምንም አይነት ጥያቄ ባትጠይቁኝና ምላሽ ባልሰጥ ደስ ይለኝ ነበር።
ይሁን እንጂ '' ለመጋቢት 28 ጠቅላላ ጉባኤ ተጠራን!'' በሚል ምክንያት የተደናገራችሁ በርካታ ወንድሞቻችን ፥ የማውቀውን እንዳሳውቃችሁ በተደጋጋሚ እየጠየቃችሁኝ ስለሆነ ፣ ለመጨረሻ ጊዜ የሚከተሉትን እጅግ አጭርና ጥቅል ሀሳብ ብቻ የያዙ ምላሾችን ልሰጣችሁ እወዳለሁ!
▫የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ በወርሃ ሰኔ 2010 ዓ.ም ከተመሰረተና የቅድመ እውቅና ሰርተፍኬት ከተሰጠው ወዲህ ፣ በተሻሻለው የቦርዱ አዋጅ መሠረት አንድም ህጋዊ ጉባኤ አድርጎ የማያውቅ ድርጅት በመሆኑ ፣ ከፖለቲካ ተፅዕኖ ባልተላቀቀው ምርጫ ቦርድ ይሁንታ 'ስሙ' እስከዛሬ ቆየ እንጂ ቴክኒካሊና ከህግ አንፃር ከተሰረዘ 2 አመት ያለፈው ድርጅት ነው!
▫ጠቅላላ ጉባኤ የመጥራት ሀላፊነትና ስልጣን ያለው ፓርቲው ሲመሰረት በደምብና በመመሪያ መሠረት የተቋቋመው 45 ቋሚና 7 ተለዋጭ አባላት ያሉት ''የብሔራዊ ምክር ቤት'' ብቻና ብቻ ነው! ጉባኤው የሚመራውም በዚያን ጊዜ በፀደቀው መተዳደሪያ ደምብ መሠረት ብቻ ይሆናል! ይህንንም ቦርዱ በወርሃ ታህሳስ 2015 ዓ.ም በደብዳቤ ማሳወቁ ይታወሳል! ይህ መዋቅር ደግሞ ሙሉ በሙሉ ፈርሷል!
▫ከብዙ እልህ አስጨራሽ ትግል በኃላ ፣ ፓርቲው ግንቦት 5-6/2015 ዓ.ም ጉባኤ እንዲያደርግ ውሳኔ የሰጠውና ይህንኑ የማድረግ ስልጣን ፣ በምርጫ ቦርድ ቀና ትብብር ያገኘው ፣ 45 ቋሚና 5 ተለዋጭ አባላት ያሉት የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ (በደብረብርሃኑ ጉባኤ የተቋቋመው) ሲሆን ፣ ያ የተወሰነ ጉባኤ ሊከናወን ባለመቻሉ ምክንያትም አዲስ ጉባኤ ለመጥራት የዚህን ኮሚቴ አዲስ ውሳኔና ይሁንታ ይጠይቃል! ይህ ባልሆነበት ጥቂት ግለሰቦች ስለፈለጉ ብቻ ከአሰራርና ከደምብ ውጪ ጉባኤ መጥራት ፈፅሞ አይቻልም! ያ መአከላዊ ኮሚቴም በተመሳሳይ ተስፋ ቆርጦ እንዲበተን ተደርጓል!
▫ከፓርቲው ማእከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ ውጭ የድርጅት ንብረት ሸጦም ሆነ በማናቸውም መልኩ ከየሜዳው ሰው ሰብስቦና እንደመናሃሪያ ወያላ ''መንገደኛውን ሁሉ እየጠሩ'' ጉባኤ አደርጋለሁ ማለት ፣ በአጭሩ ''እብደት ወይም ባለቤቷን የተማመነችው ... እብሪት'' ከመባል ውጪ ፍፁም ፍፁም ወንጀልም ጭምር ነው!
▫የሚሊየኖች መሰባሰቢያና ተስፋ የነበረው ድርጅት ዛሬ እንዲህ መሆኑ አሳዛኝና ታሪክ የማይዘነጋው ጉዳይ ቢሆንም ፣ ምናልባት አዲስ የሳምሶናይት ፓርቲ ከመመስረት ወይም ደግሞ የሀገሪቱን ህግ እንደአዲስ በማሻሻል ከማመቻቸት ውጪ ''በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)'' ስም ጉባኤ ጠርቶ ፓርቲውን የማስመዝገብም ሆነ የሳምሶናይት ፓርቲ አድርጎ የመቀጠል ስልጣን ያለው አካል የለም!
''ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ '' የተሰኘው ተቋምም ፣ ምንም እንኳ የገዢው መንግስት አንድ እጅ መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ቢሆንም ፣ እንዲህ አይነቱን የህወሓት ዘመኖቹ እነመርጋ በቃናና አዲሱ ገ/እግዚያብሔር እንኳ ያልተፈፀመ ፣ ህገ-ወጥ ብቻ ሳይሆን ''ወንጀል'' ጭምር የሆነን ጉዳይ የሚተባበር መስሎ አይታየኝም!
ጉዳዩን ስለጠየቃችሁኝ 'ለአወይ ጉዱ' አነሳሁት እንጂ ቦርዱ እስካሁን ሳይሰርዝ እንዳቆየው ሁሉ ፣ በትውልዱ ብራንድ የፓርቲ ስም ፣ ለጥቂት ግለሰቦች ሰርተፍኬት አትሞ ቢሰጥም እኛ ምን አገባን!
ምክንያቱም ፦ ውጤቱ ለጥቂቶች ኑሮ መግፊያ ከመሆን በዘለለ ''ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ'' ነውና!
ዘሪሁን ገሰሰ የአብን ከፍተኛ አመራር

የኢቢሲ በአራት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሰራተኞች ላይ የጠየቀው የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ በፍርድ ቤት ተፈቀደለት!
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ፖሊስ “በሽብር ወንጀል ጉዳይ ጠርጥሬያቸዋለሁ” ባላቸው አራት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞች ላይ የ14 ቀናት የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ። ባለፈው አርብ ፍርድ ቤት ከቀረቡ የጣቢያው ሰራተኞች መካከል፤ የካሜራ ባለሙያ የሆነው አቶ ቶማስ ደመቀ ከእስር ተለቅቋል ተብሏል።
የአቶ ደመቀን ከእስር መለቀቅ ከፖሊስ የምርመራ ምዝገባ መረዳቱን የገለጸው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ነው። ችሎቱ የኢቤኤስ ሰራተኞች የተካተቱበት የስምንት ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ መመልከት የጀመረው ባለፈው አርብ መጋቢት 19፤ 2017 ነበር።
የፌደራል ፖሊስ ለችሎቱ ባቀረበው የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ማመልከቻ ላይ በተጠርጣሪዎቹ ላይ እያካሄደ ያለውን ምርመራ “በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በስፋት ለማጣራት” የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ ነበር። ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ በዛሬው ዕለት ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ከመስጠቱ አስቀድሞ፤ የፖሊስ ጅምር የምርመራ መዝገብ እንዲቀርብለት ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።
ችሎቱ ዛሬ ሰኞ መጋቢት 22 ከሰዓት በነበረው ውሎው፤ ተጠርጣሪዎቹን በሽብር ወንጀል ለመጠርጠር አመላካች የሆኑ ነገሮች ከፖሊስ ምርመራ መዝገብ ተመልክቼያለሁ ብሏል። የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች፤ ደንበኞቻቸው ቢጠረጠሩ እንኳን “የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣ አዋጅ ስር ባሉ ድንጋጌዎች” እንደሆነ ያቀረቡት መከራከሪያ “የተፈጸመ ጥፋት መኖሩን” የሚያሳይ እንደሆነ ችሎቱ በተጨማሪነት ጠቅሷል።

በዚህ ሰአት ሰበር የተባለ መረጃ ተሰምቷል
join በዚ LINK ግቡ👇
👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
join በዚ LINK ግቡ👇
👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
የአማራ ፋኖ በጎጃም ወታደራዊ ኮማንድ “ዘመቻ አንድነትን” በተመለከተ ወቅታዊ ሪፖርት!
#Amhara#Ethiopia
የቲክቶክ ቻናላችን➲ tiktok.com/@amhara_gion
#Amhara#Ethiopia
የቲክቶክ ቻናላችን➲ tiktok.com/@amhara_gion
“እስካሁን ላጠፋነው ይቅርታ!”
በሸዋ የሚንቀሳቀሱ የ7 ለ70 ብርጌድና የይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦር ፋኖዎች ወደ አንድ የመጡ ሲሆን ከዚህ በፊት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ህዝባችንን ስለበደልን ህዝቡ ይቅር እንዲላቸው በታላቅ ትህትና ተንበርክከው ይቅርታ ጠይቀዋል።

«...ጉዳዩን አጣርተንና መርምረን ስንጨርስ ይፋ እናደርጋለን!» -ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ወልደስላሴ
የእሑድ መልዕክት በብርቱካን ጉዳይ!
በብርቱካን አንደበት የተነገረው ታሪክ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ሐዘን የቀሰቀሰ፣ በውስጣቸው ያለውን ቁጭት፣ በደል መጠቃት እና መገፋት ያስታወሰ የሴቶች እህቶቻችንን ቁስል ያስታወሰ ነው። እኔ እና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ወልደሥላሴም ታሪኳን እደሰማን የተሰማን፣ አሁንም የሚሰማን ከዚህ ጥልቅ ሐዘን የተለየ አይደለም።
በአብይ አሕመድ አገዛዝ ቁጥጥር ስር በሚገኙ ሚዲያዎችና፣ ከአገዛዙ ፍርፋሪ በሚጣልላቸው ዱሮም የአንድም ኢትዮጵያዊ፣ በተለይም የአማራ ሴቶች ቁስል ለማይሰማቸው ሁሌም በሚሰፈርላቸው ቀለብ ልክ በሚጮሁ አፎች የተነገረው ደግሞ እጅግ አደናጋሪና አወናባጅ ነው።
የአብይ አሕመድ አገዛዝ መርህ ውሸት እና ማደናገር መሆኑን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማሳወቅ እኛ መጻፍ ወይም መናገር አያስፈልገንም። ዜጎችን መጠበቅ ሲገባው፣ ለፖለቲካ ትርፍ ማግኛ እንዲውሉ ለማድረግ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲጠቁ ካደረገ በኋላ፣የደረሰባቸው በደል እንዳይጋለጥና በተጨማሪም ከበደላቸው ለማትረፍ የሚሄድበት ርቀት ከዚህ ቀደም በብዙ ሚሊዮኖች ጉዳይ የታየ ሀቅ በመሆኑ፣ እሱን ታሪኩን ለሚያውቀው ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማስረዳት ጊዜ አናባክንም።
በቆርጦ መቀጥል እና ድምጽ የማዘዋወር ሴራውም፣ የአብይ አገዛዝ ስልጣን ላይ ከመጣ ጊዜ ጀምሮ፣ ገመናቸው ተገልጦ በደፋሪዎች ክብራቸው የተገፈፈ፣ የተዋረዱ፣ የተደፈሩ፣ በአሰቃቂና ዘግናኝ ሁኔታ የተገደሉ፣ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የተጣሉ፣ የተገፉ፤ የተዋረዱና የመኖር ህልውናቸው በተገፈፉ ሴቶች ቁስል ላይ አፊዟል። አጫፋሪዎቹም አብረው አፊዘዋል።
በእዚህ ጉዳይ ያነባችሁ ያዘናችሁ እና ያለቀሳችሁ ውድ የአማራ ልጆች!
እኔና ተስፋዬ ወ/ስላሴ የምናውቀው እውነት እና እኛ ከምናውቀው እውነት ጀርባ የተሸረበው ሴራ ምን እንደሆነ በሚገባ ሳንረዳ እጃችን ላይ የሚገኙ መረጃዎችን ይዘን አደባባይ መውጣቱ፣ ማንን እንደሚጠቅም እና ማንን እንደሚጎዳ በሚገባ ሳንረዳ ራሳችንን ለመከላከል ስንል ብቻ አደባብይ መውጣትን አሁን ተመራጭ ሆኖ አላገኘነውም። ሁሌም ቢሆን ከራሳችን ይልቅ የሚይሳሳስበን ብዙ ዋጋ የከፈልንበት የአማራ ትግል እና የሕዝባች ቁስልና ጉዳት ነው።
ከዚህ ቀደምም፣ አሁንም ወደፊትም የሕዝባችን ጉዳይ ያሳስበናል። ልክ እንደኛው ሁሉ ይህ የሚያስጨንቃችሁ ብዙዎቻችሁ አገዛዙ እየሰራ ካለው ድራማ ጀርባ ያለው እውነታ ምን እደሆነ ለማወቅ ያላችሁን ፍላጎት አሳይታችሁናል። እጃችን ላይ ያለው መረጃ በአግባቡ ሰንደን ጉዳዩን አጣርተን እና መርምረን ስንጨርስ፣ ይፋ እናደርጋለን። ለአሁኑ ግን ይህ እመራዋለሁ በሚለው በዜጎቹ ስቃይ ለሚቆምር ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታው ለማታውቀው ጨካኝ መሪና አጫፋሪዎቹ መቀለጃ እንዲሆን የምናውለው ታሪክ የለም።
እውነት ተሸፍና አትቀርም፣ የተሰቃዩት እህቶቻችን ታሪክ ቀኑ ሲደርስ በፍትህ አደባባይ ይወጣል። በዳዮቻቸውና ተባባሪዎቻቸውን የእጃቸውን ያገኛሉ። በተረፈ የአገዛዙን የቅጥፈት ታሪክ እያወቃችሁ እኛን የጉዳዩ ባለቤት ለማድረግ ልሃጫችሁን የምታዝረበርቡ ሰዎች ጉዳዩ የደመወዝና የቅናት መሆኑን ስለምረዳ ይቅር ብያችኋለሁ። ይኸው ነው!

ይህ የንግድ ቢሮው ባንኮች እስከ 3 ሰዓት ድረስ ክፍት እንዲሆኑ የሚያዘው ደብዳቤ ነው። ጥያቄው ድርጅቶች ለሰራተኞች ተጨማሪ ሰዓት እንዲሰሩ ሲደረግ ለሰራተኞች ክፍያ ይጨመራል ወይስ በበፊቱ ደመወዝ ነው?
#Amhara#Ethiopia
የቲክቶክ ቻናላችን➲ tiktok.com/@amhara_gion
#Amhara#Ethiopia
የቲክቶክ ቻናላችን➲ tiktok.com/@amhara_gion
በዚህ ሰአት ሰበር የተባለ መረጃ ተሰምቷል
join በዚ LINK ግቡ👇
👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
join በዚ LINK ግቡ👇
👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
መሰልጠን፣ መታጠቁ ቀጥሏል!
የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለጦር ለወራት ያሰለጠናቸውን ስፔሻል ኮማንዶዎችን ዛሬ አስመርቋል!
#Amhara#Ethiopia
የቲክቶክ ቻናላችን➲ tiktok.com/@amhara_gion
የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለጦር ለወራት ያሰለጠናቸውን ስፔሻል ኮማንዶዎችን ዛሬ አስመርቋል!
#Amhara#Ethiopia
የቲክቶክ ቻናላችን➲ tiktok.com/@amhara_gion
በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሁለት ህጻናት ተገደሉ!
በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ትናንት ምሽት የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሁለት ህጻናት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ። ፖሊስ “በቡድን የተደራጁ” ያላቸው አካላት በወረዳው ዘይሴ ወዘቃ ቀበሌ ግድያውን የፈጸሙት ህጻናቱን በቤት ውስጥ አስገብተው በመቆለፍ በእሳት እንዲቃጠሉ በማድረግ ነው ብሏል ፡፡
ሕይወታቸው ያለፈው የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ የአራት እና የሰባት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህጻናት መሆናቸውን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሰላም እና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኮሜ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል፡፡ በህጻናቱ ላይ የፈጸሙት ጥቃት “ዘግናኝ ፣ ከሰብአዊነት ያፈነገጠ እና አረመኔያዊ ነው” ያሉት አቶ ኮሜ ጥቃት አድራሾቹ በዛው ቀበሌ በአንድ የወረዳ አመራር መኖሪያ ቤት ላይም የተኩስ ሩምታ ከፍተው እንደነበር ገልጸዋል። በጥቃቱ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም “በመኖሪያ ቤቱ ላይ ግን መለስተኛ ውድመት አድርሰዋል” ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት የጋሞ ዞን እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፀጥታ አካላት በአካባቢው ተሠማርተው የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለመያዝ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ እስከአሁን ከዋንኛ የድርጊቱ ተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ የተያዘ ሲሆን ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እየተሠራ መሆኑንም ኃላፊው ጠቅሰዋል፡፡ (DW)

ሰበር ዜና!
ከነገ ሰኞ ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና ፌደራል ፖሊስ ወደ ትግራይ ክልል ከተሞች እንደሚገባ የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ። የፌደራል መንግስቱ ለዚህ ውሳኔ የደረሰው ከትላንቱ በጀነራል ታደሰ ወረደና በጠ/ሚር አብይ አህመድ ውይይት በተደረሰ ስምምነት እንደሆነ ነው ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው።
የትግራይ ይሄ ህዝብ ከሻዕብያና ከሻዕብያ ተላላኪ ሽብር ፈጣሪ ቡድኖች ለመከላከል የፌዴራል ፖሊስ ና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በዋና ከተማ መቐለ፣ ዓዲግራት፣ ዓድዋና ሽሬ ዜጎችን ዋስትና ለማረጋገጥ ሙሉ ሀይል ይገባሉ።

ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በጽናት አደረሳችሁ!
-የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ) ዋና ሰብሳቢ ዋርካው ምሬ ወዳጆ
ረመዳን በሙስሊሞች ዘንድ የጾም፣ ጸሎት ወር ነው፡፡ ረመዳን ከአምስቱ የእስልምና ማዕዘናት ዉስጥ አንዱ ነው። ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ ምትጠልቅ ድረስ መጾም ለአቅመ አዳም (ሄዋን) ለደረሱ ሙስሊሞች ፋርድ (ግዴታ) ነው። ሙስሊሞች ብዙ ጊዜን በጸሎት፣ በሰላት እና በሰደቃ(ምጽዋት) እንዲሁም ስነ ምግባራቸውን ለማሻሻል በመጣር ያሳልፋሉ። ይህም ረመዳን ሲደርስ የገነት በሮች ይከፈታሉ፣ የሲኦል (ገሃነም) በሮች ይዘጋሉ እና ሰይጣናት ይታሰራሉ።
እኛም የአማራ ፋኖ በዱር በገደል በርካታ ውጣ ውረዶችን እያለፈ ለመላው የአማራ ሕዝብ የተከፈተውን የሲኦል በር ለመዝጋት መላው ሰራዊታችን አጥንቶ እየከሰከሰ ነባር እምነቶችን፣ ባህሉን፣ ማንነቱን ለማስከበር እየተዋደቀ ይገኛል። አሁን ላይ አማራዎችንና አማራነት የገጠመው ጠላት ዘር በመለየት ሙስሊም አይል፣ ክርስቲያን ሁሉንም በከባድ መሳሪያ፣ በሰው አልባ አውሮፕላን እየጨፈጨፈ ይገኛል።
ትናንት በወለጋ “ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም” እያለች ከተገደለችው የሰባት አመት ህጻን ጀምሮ ዛሬም በተኛንበት አልጋ ላይ ከህጻን እስከ አዋቂ፣ ከመንግስት ሰራተኛ እስከ ገበሬ፣ ከእስልምና እስከ ኦርቶዶክስ በአማራነታችን እየጨፈጨፈን ይገኛል። ስለሆነም መላው የሙስሊም እምነት ተከታዮች በብዙ ፈተና ውስጥ ብትሆኑም አንድ የማይተካ ሕይወቱን የሚሰጥ የአማራ ልጅ ፋኖ ተወልዶልሃልና እንኳን ደስ አለህ ማለት እፈልጋለሁ።
በመቀጠል ትናንት ከእነ መሀመድ ቢሆነኝ እና ጓዶቹ ጋር ሁኜ የጀመርሁትን ትግልና አደራ በድል እንደምንቋጨው በሙሉ ልቤ መግለጽ እፈልጋለሁ። በዱር በገደል እየተዋደቃችሁ ላላችሁ ለመላው የአማራ ፋኖ ለእስልምና እምነት ተከታዮች፣ ለመላው የአማራ ሙስሊሞች እና ለመላው ሙስሊሞች ኢድ ሙባረክ እንኳን በጽናት አደረሳችሁ እያልሁ፣ በዓሉን ስናከብር ነብዩ እንዳሉት “ከሰደቃ በላጩ የረመዳን ሰደቃ ነው፤ “ጀነት ውሰጥ ውጪው ከውስጥ ውስጡ ከውጭ የሚታዩ ክፍሎች አሉ” ሲሉ “አንቱ የአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ለማን ናት? (ለማን ነው የምትሰጠው)” ተባሉ ነቢዩም “ንግግሩን ላሳመረ፣ ምግብ ላበላና ፆምን ላዘወተረ፣ ሰዎች ተኝተው በሌሊት ለሰገደ ነች።” እንዳሉት አስተምህሮውን በጠበቀ በዓሉን እንደታከብሩ ማስታወስ እፈልጋለሁ።
በድጋሚ ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 1446ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በጽናት አደረሳችሁ። ኢድ ሙባረክ!

እስካሁን ከ1700 በላይ ሰዎች ሞተዋል!
በሚያንማር የተከሰተውን ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ እስካሁን ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ በላይ ሰዎች መሞታቸውን ቢቢሲ ዘግበቧል።
#Amhara#Ethiopia
የቲክቶክ ቻናላችን➲ tiktok.com/@amhara_gion
በሚያንማር የተከሰተውን ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ እስካሁን ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ በላይ ሰዎች መሞታቸውን ቢቢሲ ዘግበቧል።
#Amhara#Ethiopia
የቲክቶክ ቻናላችን➲ tiktok.com/@amhara_gion
ኢድ-ሙባረክ!
ለአማራ ህዝብ መብት መከበር ስትሉ በዱር ገደሉ የምትዋደቁ ሙስሊም ፋኖዎች መልካም ኢድ-ሙባረክ ይሁንላችሁ!