Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።
ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።
ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!
Recent Posts
ደግ አደረጓችሁ‼
«ተዘረፍን!
ዘግተው ጠፉ!
መንግስት ይድረስልን ህዝብ ድምፅ ይሁነን
1.AIM ULTRA EDUCATIONAL CONSULTANCY PLC
2.KABBA HOLDING COMPANY
3.TRIPX CONSULTANCY
4.PESCO PEST SOLUTION
5.BLUE LINK CONSULTANCY SERVICES
6.JOB LINK MAN POWER SOLUTION COMPANY
7.YELLOW CARD ONLONE WORK CONSULTANCY
8.ATOMIC CONSULTANCY እና ወዘተ
9.Ruby consultancy service
10.A3tour consultancy
ከላይ ስማቸዉ የተዘረዘሩት ድርጅቶች መቀመጫቸዉ አዲስ አበበ የሆኑት ሲሆን ድርጅቶቹንም የሚያንቀሳቅሱት ወ/ሮ ቤቴልሔም ታደሰ የተባሉ ግለሰብ ናቸዉ።
ከስማቸዉ እንደምንረዳዉ የድርጅቶቹ አላማ ለ አገልግሎት አገልግሎት ፈላጊዉ በማህበራዊ ጉዳይ የቪሳ ማማካር እና ሰነድ የማደራጀት ስራ ለመስራት የተቋቋሙ ሲሆን ነገር ግን የተቋቋሙበትን አላማ ወደ ጎን በመተዉ ወጣቶችን በመዝረፍ ላይ ይገኛሉ።
በቅድመ ክፍያ (በዱቤ) ወደ ተለያዩ ዉጭ ሀገሮች
🇨🇦ካናዳ
🇷🇴ሮማኒያ
🇷🇺 ሩሲያ
🇧🇾ቤላሩስ
🇵🇱ፖላንድ
ወ ዘ ተ
እንልካችዋለን በማለት በተለያየ ጊዜ ወጣቶችን በማታለል ከወጣቶቹ ብር እየዘረፉ ይገኛሉ። ተገልጋዩ አገልግሎቱን ሳያገኝ ስቀር በውለታዉ መሰረት የከፈለዉ ገንዘብ ድርጅቱ እንድመልስለት በወጣቱ ላይ ግርፊያ፣ድብደባ እና የድርጅቱን ስም በመቀየር ይህንን የሚባል ደርጅት አለውቀዉም የሚል መልስ ይሰጣሉ።
ይህንን ሲያደርጉ ግን ወጣቱ በ ዲሲፕሊን ከመጠየቅ ውጪ አንድም ያደረገ የለም።
በዚህ ጉዳይ ላይ በተለያየ ጊዜ ለመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ለፀጥታ ሀይሎች፣እንዲሁም ለታዋቂ ሰዎች አቤቱታ እያቀረበ ቢገኝም ገንዘቡ እስካሁን አልተመለሰም።
ይህ ድርጅት ከ አዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ፅ/ቤት የንግድ ፍቃድ በመዉሰድ እየዘረፈን ይገኛል።
በስሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ Sales ሰራተኛ ቢኖሩትመረ በዋናነት ይህንን ድርጊት የሚፈፅሙ ግለሰቦች:-
1. አቤል ተስፋዬ
2.ቤትልሔም ታደሰ
3. ገሊላ በለጠ
4.ዳዊት በለጠ
5.ሩት መኮንን
6.ልዲያ መኮንን
7.ወንድወሰን ላቀዉ እና
8. ሀብታሙ
10.ሊዲያ መኮንን የሚባሉ ግለሰቦች ናቸዉ።
የ አ/አ ከተማ እነኚህ ግለሰቦች ላይ አስተዳደራዊ እና የሚያስተምር እርምጃ እንድወስድልን የበኩላችሁን ድርሻ ተወጡልን
ተብዳዮች: ጉርሻ»

ጫት ቃሚ ሰው ለብዙ ወንጀሎች ሊጋለጥ ይችላል። ጫት መቃም ቀስ በቀስ ሲጋራ ወደማጨስ ያመራል፣ ሲጋራ ወደ ሺሻ፣ ሺሻ ወደ አስካሪ መጠጥ፣ አስካሪ መጠጥ ወደ ዝሙት ያመራል። ታዲያ ሰው ምን ቀረው ይህን ካደረገ!
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️
[Part: ⓵⑨⑨③]👌
#ቁርኣን
[Part: ⓵⑨⑨③]👌
#ቁርኣን
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️
[Part: ⓵⑨⑨②]👌
#ቁርኣን
[Part: ⓵⑨⑨②]👌
#ቁርኣን
ስሚ እህቴ…
ከባልሽ ጋር ተጣጥመሽ መኖር ካልቻልሽ፣ ጉዳዩ በውይይትና በምክክር መፈታት ካልቻለ፣ ወይም ታግሰሽ መኖር ካቃተሽ፤ ለስሙ ባል አለሽ ተብለሽ ዝሙት እየሠራሽ ከምትኖሪ መፋታቱ ይሻላል። አላህን ፍሩ! በባል ላይ ሌላ ባል አይያዝም፣ ባልጋችሁ ሰው አታባልጉ። በላእ ሳይወርድባችሁ፣ ከአላህም ጋር ከምትጣሉ… እየከበደም ቢሆን ተፋቱና ካገኘሽ የተመኘሽውን አግቢ። ብቻ ግን ከአላህ ጋር ከሚያጣላ ነገር ራቂ።
አንተም ወንድሜ፦
ካልተመቸችህና ለማስተካከል ጥረህ ካልተሳካ አቅም ካለህ ሌላ የምትፈልጋትን ጨምር እንጂ በሐራም አትጨማለቅ። ለተጨማሪ አቅም ከሌለህ ከመጨማለቅ ያቺን ፈተህ ሌላ አግባ። መቼም ከዝሙት ይሻላል።

በነገራችን ላይ አንዳንድ ኡስታዞች እንደ ቲክቶክ ያሉ ሶሻል ሚዲያዎችን ባይጠቀሙ አሪፍ ይመስለኛል። ለዳዕዋ አላማ ብለው በዛው እንዳይሳሳቱ ብዬ ነው! ማለቴ ነፍሱን እስከ ጥግ የቆጠበ ጀግና ካልሆነ ቀስ በቀስ ሳያስበው ሊሟሟ ይችላል። ከዛ ካዩ በኋላ በዝርዝር ያዩትን ነገር እየተረኩ «እንዲህ እንዲህ የሚያደርጉ ሴቶችን አላያችሁም ወይ? ሱብሐነ-ል'ሏህ! ሀዛ ሐራም…» ቢሉት ጥሩ ላይመጣ ይችላል። በደፈናው የሚወገዝ ስላለ! አሊያ «የት አየኸው አንተስ?» ሊያስብል ይችላል።
እና ደግሞ ካሜራ አጠቃቀሟን ምናምን በደንብ ሳታውቁባት የምታስተላልፉት ጥሩ ነገር ቢሆንም የሆነ መጃጃል ነገር ስለሚመስል ወይ በዘርፉ የሚያውቁ ሰዎችን ጠይቁና በአግባቡ ተጠቀሙ። ነገሮችን ካስተካከላችሁና ራሳችሁን ካቀባችሁ፤ በቦታው መኖራችሁ ወሳኝ ነው። ግን ደግሞ አንዳንዱ ራሱን የማይቆጣጠር ለናንተ ብሎ ቲክቶክ ገብቶ በዛው ተዘፍቆ ሊቀር ይችላል።

ምንጣፉ ራሱ ስታየው ልዩ ስሜት አለው!
«بسم الله
-ቂርዓት ላይ ያለሽ እህት ሆይ .... ኢልም መቅሰም ሂወትሽን ሙሉ የምትሰጭዉ ዉድ ነገር ይሁን እንጂ እስክታገቢ ወይም ሀገር ቤት እስክትገቢ ጊዜ ማሳለፊያ አታድርጊዉ ።
- ሴት መሆንሽ ኣሊማህ ከመሆን አያግድሽምና በኢልም ትልቅ ደረጃ እደርሳለሁ ብለሽ ለነፍስሽ ንገሪያት ሂማሽን በጣም ከፍ አድርጊ ለዚህም የሴት ምሁራኖች ታሪክ ማንበብ ይረዳሻል ።
አንጋፋው የአል-ሃፊዝ ኢብኑ ሀጀር ተማሪ አል-ኢማም السخاوي ከ80 በላይ ሸይኻዎቹ ሴቶች እንደ ነበሩ( بين فقيهة ومسندة) ታዉቂያለሽ ????
-ከአመት አመት አጫጭር ኪታቦች ብቻ አትቅሪ ይልቁን በቅደም ተከተል ከሙኽተሰር ኪታቦች አንስተሽ እስከ ሰፋፊ ኪታቦች መቅራት አለብሽ በዚህም ነዉ እዉቀትሽን የምታዳብሪዉ ብዙ እህቶችንም በፈትዋ ምታብቃቂዉ
ለምሳሌ ዘንድሮ ሰፊና እየቀራሽ ከሆነ የዛሬ 3 or 4 አመት ሚንሃጅ መጨረስ አለብሽ አቂዳም እንደዚሁ ፈትሁል መጂድ ምናምን ማጠናቀቅ አለብሽ ሌሎች ፈኖችም ላይ እንደዚሁ ።
በዚሁ አደራ ምልሽ ያለአቅምሽ ያልደረስሽበትን ፈን ወይም ኪታብ አትዳፈሪ فإنه من رام العلم جملة ذهب عنه جملة .
-ምንም ቢያነሳሱሽም በሱና ሰዎች መሀከል ባለ ልዩነት እራስሽ ቢዚ አታድርጊ ።
-ጎደኞችስ አንቺን የሚመስሉ ለቂርዓት ትኩረት የሚሰጡ እንጂ በተራ ወሬ ዉድ ጊዜያቸውን የሚያባክኑ አይሁኑ።
بالله التوفيق»
©: ዐብዱ-ር'ረዛቅ ባጂ

የሐላል ርቀት‼
===========
«ብዙው የተማረ ሰው በቅጥር ደሞዝ የትም ስለማይደርስ በአማካሪነት ተመራማሪነት ይቀጠራል ይሰራል። ወይም ወደፖለቲካ ዘው ብሎ ይገባል። የሚያሳዝነውና አስከፊው ነገር በገባበት አለም ራሱን ሞራሉን ጥሎ እንጂ አብዛሀኛውን ጊዜ ያሰበውን ነገሮች ማግኘት አይችልም።
ሰሞኑን የ አለም ጤና ድርጅት አማካሪ ኮንሰልታት ፈልጎ ማስታወቂያ አውጥቶ ነበርና እንደለመድኩት አለሁ አልኩ። እና ፎርሙ ላይ በርካታ ባይበላስ የሚያስብሉ፣ አላህ ጋር የሚያጣሉ ጥያቄዎችን እስማማለሁ እያልክ ማለፍ አለብህ። ገና ሲጀምር ራሱ ጾታ ላይ ምርጫው ራሱ አምስት አይነት ነው። ከዛ ኋላ ያለውማ ዘግናኝ ነው...በሊዋጢ ነጻነት ታምናለህ ስትባል yes!
ሌላው ደግሞ ይሄን ሁሉ ሀራም ይሁን ብለህ ስራውን ካገኘህ በኋላ የሚመጣው ነገር ነው። ከ ጥቂት አመት በፊት አንዱ የ UN ድርጅት Subsaharan Africa ላይ ስለሰሩት ስራ ለህብረተሰቡ ያመጣውን ጥቅም ለመገምገም ተመራማሪ ፈልገው ለምስራቅ አፍሪካ እኔን ቀጠሩኝ። እናም ስራውን ሰርቼ draft report አስገባሁ። እናም ውጤቱን ያነበቡ አሰሪዎቼ በውጤቱ ተቆጡና ስብሰባ ጠሩ። እስከ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ያሉ አባሎች በእንጀራችን መጣህ ብለው ሊበሉኝ ተሰበሰቡ። ውጤቱን አቅርብ ተባልኩና ድርና ማጓን ሳይቀር ብትንትን አድርጌ አስረዳሁ። ውጤቱ ምን ሆኖ ነው ካላችሁኝ፤ የሰራችሁት ስራና ያወጣችሁን ሚልየን ዶላሮች ያሰባችሁትን ውጤት አላመጣም በማለቴ ነበር። አሻሽል ቢሉኝም ደረቅኩ። እነሱም ተስፋ ቆርጠው በአጭሩ ብሬን ሰጠው አሰናበቱኝ። ከዛ ጊዜ በኋላ እዛ ድርሽ አላደረጉኝም!
አንዳንዴ ሀኪም ሆነህ ስትሰራ በሽተኛው ምን እንዳመመው በቀላሉ ታውቃለህ። በቀላሉም እንዴት እንደሚታከም ትረዳለህ። ሆኖም ክሊኒኩ ኪራይ ነው፣ ግብርም፣ የሰራተኛም ደሞዝ አለ። በቃ ሽንት ደም ሰገራ ራጅ ሁሉም ይታዘዛል.....ወይ ጣጣ
ብዙ ነጋዴዎች ጉቦ ይሰጣሉ። እናም ሸር ለመግፋት ነው ይላሉ። ጉቦ ካልሰጠ ትራፊኩ አይለቀው፣ ግብር አይቀነስለት፣ ቤቱ ስም አይዘዋወር...መገን ጣጣ
አህባቦች ሀላል መብላት ቀላል አይደለም። ገቢ አነሰን የምትሉ ሁሉ ሀላል ከሰጣችሁ ትልቅ ውለታ ነው። እንደው በደፈናው አላህ ይሁነን!»
©: ፕሮፌሰር ቃልኪዳን ሐሰን

[Part: ⓵⑨⑨①]👌
#ቁርኣን
[Part: ⓵⑨⑨①]👌
#ቁርኣን
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️
[Part: ⓵⑨⑨∅]👌
#ቁርኣን
[Part: ⓵⑨⑨∅]👌
#ቁርኣን
አየህ?
ፈተና መድኃኒት ነው። አላህ ሲፈትንህ መድኃኒት እየሰጠህ ነው። ፈተና ባይኖር ኖሮ ሰዎች የበለጠ ድንበር ያልፋሉ።

ሰው ለሃይገርና ቅጥቅጥ እንዲሁም ለባስ ተሰልፎ ሳለ እናንተ በመኪና ስታልፉ «አ-ስ'ሰላሙ ዐለይኩም» ሲላችሁ የማትመልሱ ሰዎች፤ ቀጣይ ቀን ግን ቆንጆ መኪና ይዞ ሲያልፍ ስትመለከቱ አሳዳችሁ «አ-ስ'ሰላሙ ዐለይኩም» የምትሉ… ጥሩ ነው ወይ ይሄ ነገር? መኪናው የርሱ ይሁን የሌላ መሆኑን እንኳ ሳታጣሩ'ኮ ነው! ለማንኛውም ሰው በማንነቱ እንጂ በቁስ አይለካም። አሁን ላይ ለአላህ ብሎ አንድን ሰው ከመውደድ ይልቅ ለጥቅም መቀራረብ እየበዛ መጥቷል። አላህ ይጠብቀን!